ሀገሬ ቲቪ

የእስራኤል ጦር በዌስት ባንክ ከፍተኛ ዘማቻ ጀምሯል

የእስራኤል መከላከያ ከትናትት ጀምሮ በዌስት ባንክ ባሉ በርካታ ከተሞች ከፍተኛ ነው የተባለለት ወታደራዊ ዘመቻ እያካሄደ ነው።

የእስራኤል ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ወታደሮቹ ኢላማ ያደረጉት በኢራን የተቋቋመውን ለሽብር ድርጊት የሚውሉ መሰረተ ልማቶችን ማምከ ላይ ያለመ መሆኑን ጠቁመዋል።

በወታደራዊ ዘመቻው 11 የሚሆኑ ፍልስጤማውያን መገደላቸውን የፍልስጤም ጤና ሚኒስቴር ሲናገር እስራኤል በአንፃሩ በኢራን የሚደገፈው ሃማስ ሌላ የጦር ግንባር እንዲፈጠር እየጣረ ነው ሲል ከሶታል።

በጦርነቱ ሳቢያ በተፈናቀሉ ፍልስጤማውያን ሕፃናት መካከል ተላላፊ የሆነ የቆዳ በሽታ መከሰቱ ተሰምቷል።

በአስናቀ ማናዬ
2024-08-28