
ብሔራዊ ባንክ ነሐሴ 21 ቀን 2016 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ የወርቅ አምራች ኩባንያዎች ወርቅ ሸጠው የሚያገኙትን የውጭ ምንዛሪ ለሶስት ወራት ይዘው እንዲጠቀሙበት መመሪያ ፈቅዷል።
ባንኩ አክሎም ወርቅ አቅራቢዎች ባንድ ጊዜ ከ250.01 ግራም እስከ 25 ኪሎ ግራም ወርቅ ለሚያቀርቡ ብሔራዊ ባንክ ወጪያቸውን የሚሸፍን እንደሆነ ተገልጿል።
እንዲሁም ወርቅ አቅራቢዎች ላቀረቡት ወርቅ 95 በመቶ ክፍያ በቅድሚያ በመውሰድ ቀሪውን 5 በመቶ ዋጋ መጠበቂያ በማድረግ ወርቁን ለግዢ ማዕከላት ካስረከቡበት ቀን ጀምሮ በ30 ተከታታይ ቀናት ከተመዘገበው ዋጋ መርጠው በሚያቀረቡት ዋጋ ክፍያቸውን እንደሚያገኙም ባንኩ አስታውቋል።
በናርዶስ ታምራት
2024-08-28