
በዳታ ማይኒንግ ስራ ላይ ለተሰማሩ ድርጅቶት በጠየቁት የኃይል ፍላጎት መሠረት በቂ ኃይል ማቅረብ አለመቻሉን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ።
በዚህም ሳቢያ በበጀት ዓመቱ በዕቅዱና በአፈፃፀሙ መካከል ክፍተት መስተዋሉን ተቋሙ ተናግሯል።
በበጀት ዓመቱ በዳታ ማይኒንግ ሥራ ላይ ለተሰማሩ ድርጅቶቹ 882 ነጥብ 48 ሚሊዮን ጊጋ ዋት ሰዓት ኃይል በማቅረብ 27 ነጥብ 71 ሚሊዮን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ እንደነበር ተነግሯል።
ይሁን እንጂ 796 ነጥብ 28 ሚሊዮን ጊጋ ዋት ሰዓት የኤሌክትሪክ ኃይል በማቅረብ ከ25 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ተገኝቷል ተብሏል።
ይህም ከዕቅዱ አንፃር ከ90 በመቶ በላይ ማሳካት መቻሉ መናገሩን ከተቋሙ ማህበራዊ ትስስር ገፅ ተመልክተናል።
በብሩክታዊት አሥራት
2024-08-28