በስልጤ ዞን ከ6 ሺ በላይ ሰዎች መፈናቀል ምክንያት የሆነው የጎርፍ አደጋ ዘላቂ መፍትሄ እንዲሰጠው ነዋሪዎች ጠየቁ።
ሰሞኑን ስልጤ ዞን ስልጢ እና ምስራቅ ስልጢ ወረዳዎች ከ6 ቀበሌዎቸ በላይ የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው የጎርፍ አደጋ እስከሁን ከ9 መቶ በላይ ቤቶች በጎርፍ ሲዋጡ፤ ከ6 ሺህ በላይ ዜጎች ለከፋ አደጋ ተጋልጠዋል፡፡
በአደጋው ምክንያት ከ1 ሺ 200 ሄክታር በላይ የበቆሎ፣ ስንዴ፣ ማንጎ፣ ፓፓያ እና ቡና ምርት ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጭ መሆኑን ዞኑ አስታውቋል።
በአከባቢው በበጎ ፍቃድ የተሰማሩ ወጣቶች፤ ወረዳው ዞኑ ድጋፍ እየደረገ ቢሆንም የተጎጂ ህዝብ ቁጥር ከፍተኛ በመሆኑ መላው ኢትዮጵውያን ሰብዓዊ ድጋፍ እንዲያረጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በአደጋው ሙሉ በሙሉ ንብረታቸው ያጡ የአከባቢው ነዋሪዎች የጎርፍ አደጋው ዘላቂ መፍትሄ እንዲሰጠውም ጠይቀዋል፡፡
በብሩክታዊት አሥራት
2024-08-28