ሀገሬ ቲቪ

የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች ዝርፊያ የብሄራዊ ድህንነት ስጋት ነው

ብሔራዊ የመረጃና ደኅንነት አገልግሎት በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ላይ የሚደረጉ ዝርፊያዎች የብሔራዊ ደህንነት አንድምታ ያላቸው እንደሆኑ አስታወቀ።

አገልግሎቱ በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች ላይ የሚደረጉ ዝርፊያዎችን አስመልክቶ ጥናት ማድረጉን ያስታወቀ ሲሆን፤ በጥናቱ ውጤት ዙሪያ ከፌደራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር ተወያይቷል።

በዚህ ውይይት ወቅት የሚደርሱ ውድመቶችንና አሻጥሮችን በወቅቱ በመገምገም ተመጣጣኝ እርምጃዎችን ለመውሰድ የሚያስችል ብሔራዊ ግብረ ኃይል ሊቋቋም እንደሚገባ የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ጠቁመዋል።

በእሱባለው ጋሻው
2024-08-29