ሀገሬ ቲቪ

ከ86 ሺሕ ያለፉት የዋግኽምራ ተፈናቃይ

በዋግኽምራ ዞን በግጭት ምክንያት ተፈናቅለው ወደ ሰቆጣ ከተማ የሚገቡ ዜጎች ቁጥር ከ86 ሺሕ በላይ ማለፉ ተነገረ። ዞኑን ከሚያዋስኑ 7 ወረዳዎች በሳምንት በአማካኝ ከአራት ሺሕ እስከ አምስት ሺሕ ዜጎች ወደ ዞኑ መቀመጫ ሰቆጣ ከተማ እየገቡ መሆኑን የዞኑ የአደጋ ስጋት ቅድመ ማስጠንቀቂያ አስታውቋል።

ከተፈናቃዮች ውስጥም ከ40 ሺሕ በላይ የሚሆኑት ሴቶች ናቸው። በመጠለያ ጣቢያ ውስጥ እንዲጠለሉ የተደረጉት ከ16 ሺሕ አይበልጡም ቀሪዎቹ 64 ሺሕ የሚሆኑት ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር ተቀላቅላቅለዋል።

በፍሬህይወት ታደሰ
2022-05-16