ሀገሬ ቲቪ

የአማራ ክልል ዜጎች የጦር መሳሪያ እንዲያስመዘግቡ ጥሪ አቀረበ

የአማራ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ከግንቦት 9/2014 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 4 ቀናት የጦር መሳሪያ ምዝገባ አካሂዳለሁ አለ።

ቢሮው ከዚህ በፊት ያልተመዘገበ ማንኛውም የጦር መሳሪያ የታጠቀ ግለሰብ በአካባቢው በሚገኙ የምዝገባ ማዕከላት በመገኘት እንዲያስመዘግብ አሳስቧል።

የጦር መሳሪያ ምዝገባው የአማራን ሕዝብ ደኅንነት ለማስጠበቅ አጋዥ ኃይል ለማጠናከር ያለመ ነው ብለዋል። ማንኛውም የጦር መሳሪያ ያለው ምዝገባ ካካሔደ በኋላ የተደራጀ ሥልጠና እንዲወስድም ይደረጋል መባሉን ሰምተናል።

በመቅደስ እንዳለ
2022-05-16