ከመንግሥት የልማት ድርጅቶች በዘጠኝ ወራት 439 ቢሊዮን ብር ገቢ ተሰበሰበ።
ከተጠሪ የልማት ድርጅቶች የምርት እና አገልግሎት ሽያጭ 428 ቢሊዮን ብር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ 439 ቢሊዮን ብር መገኘቱን የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታ አስተዳደር አስታውቋል።
ካለፈው ዓመት ተመሣሣይ ጊዜ ጋር ሲነጻጸር የ73 በመቶ ብልጫ ያለው ሲሆን፤ ከታክስ በፊት 46 ነጥብ 6 ቢሊዮን ለማትረፍ ታቅዶ ብር 70 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ተገኝቷል፤ ካለፈው ዓመት ተመሣሣይ ጊዜ ጋር ሲጻጸር በ32 በመቶ ዕድገት እንዳሳየ ተመላክቷል።
በፍሬህይወት ታደሰ
2022-05-16
