ዩጋንዳ በምስራቅ አፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውን የኒውክሌር ሀይል ማመንጫ መሬት ተረከበች።
በዋነኛነት በሃይድሮ ኤሌክትሪክ ሃይል ላይ የተመሰረተችው ዩጋንዳ የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅሟን በ12 እጥፍ ወደ 17 ሺሕ ሜጋ ዋት ለማሳደግ አቅዳለች።
ይህ ተግባርም ሀገሪቱ በኃይል አቅርቦት ላይ ያለባትን ክፍተት ይሞላል ተብሎም ይጠበቃል።
በአፍሪካ ብቸኛው የአቶሚክ ሃይል ጣቢያ በደቡብ አፍሪካ ኬፕታውን አቅራቢያ የሚገኝ ሲሆን ኬንያ እና ናይጄሪያ የኒውክሌር ሀይል ማመንጫዎችን ለመገንባት ውጥን አላቸው።
በመቅደስ እንዳለ
2022-05-16
