ኢትዮጵያን ለመወንጀል ሲረቅ የቆው አዋጅ ተቀባይነት ሳያገኝ ውድቅ ተደረገ። የአሜሪካ ኮንግረስ በሀገሪቱ ብሔራዊ የመከላከያ ፍቃድ ህግ ላይ ኢትዮጵያን ለመወንጀል ሲረቅ የቆውን ”የትግራይ ዘር ማጥፋት" ረቂቅ አዋጅ ማሻሻያ ተቀባይነት ሳያገኝ ውድቅ መደረጉ ተገለጸ። የፕሬዝደንት ባይደን አስተዳደር ኢትዮጵያን በጦር ወንጀለኝነት ለመክሰስ በማሰብ ለወራት በረቂቅ ደረጃ ሲያዘጋጅ የቆየውና ከሰሞኑ ሊፀድቅ የነበረው የ“ትግራይ ዘር ማጥፋት አዋጅ" ማሻሻያ ከብሔራዊ መከላከያ ፍቃድ ህግ ላይ ተወግዷል ሲል የኢትዮ አሜሪካ ልማት ምክር ቤት (EADC) በትዊተር ገጹ ለጥፏል። ውሳኔው እዚህ ደረጃ ላይ ሊደረስ የተቻለው ኢትዮጵያዊያን እና ኤርትራዊያን ብሎም ሌሎችም አፍሪካዊያን የ #NoMore እንቅስቃሴን በማቀጣጠል፤ ለአሜሪካ ኮንግረስ አባላት ስልክ በመደወል፣ ኢሜይል በመፃፍ እንዲሁም ተደጋጋሚ የተቃውሞ ሰልፍ በመውጣት ባደረጉት ከፍተኛ ተጋድሎ መሆኑን የልማት ምክር ቤቱ አስታውሷል። በተጨማሪም ምክር ቤቱ ሌሎች የሀሰት ውንጀላዎችን መሰረት አድርገው ኢትዮጵያን ለመጉዳት እየተዘጋጁ ያሉ ህጎች እስከሚቆሙ ድረስ ትግሉ ሊቀጥል እንደሚገባ አሳስቧል፡፡
በሀገሬ ቲቪ
2021-12-08
