ሀገሬ ቲቪ

አስገራሚው የውቅያኖስ ወለል

ምድራችን እጅግ አስገራሚ ነገሮችን በውስጧ ታቅፋለች።

ታዲያ ግዜ ግዜን እየተካ በመጣ ቁጥር ከዚህ ቀደም አይተናቸውም ይሆናሉ ብለን አስበናቸውም የማናውቃቸው ነገሮች ሆነዋል ሲባሉ እንሰማለን።

ታዲያ ለዛሬ ከወደ መሬት ዞር እንበል እና በውቅያኖስ ውስጥ ታየ ስለተባለ አስገራሚ ወለል እናውጋችሁ። ተመራማሪዎች በአትላንቲክ ውቅያኖስ ወለል ላይ በስርዓቱ የተሰደረ ቢጫ የወለል ንጣፎችን አገኘን ማለታቸውን ሰምተናል።

በሺዎች ከሚቆጠሩ ሜትሮች በታች በውቅያኖሱ ወለል ላይ የተገኘው ባለቀጭን መንገድ ቢጫ የወለል ንጣፍ ተመርማሪዎችን አስገርሟል።

በሰው እጅ የተበጁ ሚመስሉት ንጣፎች ተፈጥሮ በራሷ መንገድ ያበጀችው እንጂ በሰው እጅ የተዋቡ አይደሉም ባዮች ናቸው። በፍፁም፤ ካለ ሰው እጅ ጥበብ ይህን የመሰለ ንጣፍ እንዴት ሊፈጠር ቻለ? የበርካቶች ጥያቄ ነው። ታዲያ ተመራማሪዎቹም ለዚህ መልስ አለን እያሉ ነው።

በባህሩ ወለል ላይ በተደጋጋሚ ሲፈጠር በነበረው እሳተ ጎመራ ሳቢያ ይህንን መልክ ሊይዝ ችሏል ባዮች ናቸው። በእነዚህ የእሳተጎመራ ፍንዳታዎች ሳቢያም በውቅያኖሱ ወለል ላይ በርካታ የእሳተጎመራ ውጤት የሆኑ ቋጥኞች ተከማችተዋል።

ታዲያ ይህ የወለል ንጣፍ በሚሊዮኖች ዓመታት ውስጥ የመቀዝቀዝ እና የመጋል ውጤት ነው ሲሉ ተመራማሪዎቹ ምክኛቱን ለማስረዳት ሞክረዋል። ተመራማሪዎቹ ከአሜሪካው ህዋዪ ግዛት በስተ ሰሜን በኩል ያለውን የአትላንቲክ ውቅያኖስ ውስጥ ያሉትን የእሳተጎመራ ውጤቶች እያጠኑት ይገኛሉ።

ምርምሩ የውቅያኖስ ኤክስፕሎሬሽን ትረስት ናውቲለስ ኤክስፕሎሬሽን የተሰኘ ፕሮግራም አካል ነው። የምርምር ቡድኑ ዋና አላማ ከአካባቢው የባህር ውስጥ ከፍታ ቦታዎች - በእሳተ ገሞራ እንቅስቃሴ የተገነቡ የውሃ ውስጥ ተራሮች - እድሜያቸውን እና አመጣጣቸውን የበለጠ ለመረዳት የጂኦሎጂካል ናሙናዎችን መሰብሰብ ነው።

ይህንን ማጥናታቸውም በህዋይ ደሴቶች አፈጣጠር ላይ አዲስ ግኝቶችን ለማግኘት እንደሚረዳቸው ላይቭ ሳይንስ አስነብቧል። ተመራማሪዎቹ እንዳሉርት ከሆነ ከዚህ በፊት ጥናት ባልተደረገበት በዚህ አካባቢ የምናደርገው ጥናት በጥልቁ እና ጥንታዊ የባህር ውስጥ ድንጋያማ ድንጋያማ ቦታዎች ላይ ያለውን ህይወት በጥልቀት እንዲመረምሩ እየረዳቸው ይገኛል።

ታዲያ ከዚ ቀደም ታይቶ የማይታወቅ ባለትልልቅ አይን ፍጥረትን አግኝተው ለዓለም ማጋራታቸው ይታወሳል። እንደ ምዕራባውያኑ በ2018ም እንዲሁ ለምርምር በውቅያኖሱ ውስጥ በተገኙበት ወትት፤ ከአቅሟ በላይ ግዙፍ አሳን መብላት የምትችል የአሳ ዝርያን ማግኘታቸው ይታወሳል።

ታዲያ ይህ ምርምራቸው አዳዲስ ነገሮችን ለማየት እድል እንደሰጣቸው እየተናገሩም ይገኛሉ።

በሳምሶን ገድሉ
2022-05-17