ሀገሬ ቲቪ

የኢትዮ ኤርትራ የንግድ እንቅስቃሴ ጅምር

በኢትዮጵያ እና ኤርትራ የድንበር አካባቢ ንግድና የሰዎችን እንቅስቃሴ የሚያፋጥኑ ስራዎች ተጀምረዋል ተባለ፡፡

የድንበር አካባቢ ንግድና የሰዎችን እንቅስቃሴ የሚያሳልጡ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች፣ የወደብ አጠቃቀም፣ የንግድ ልውውጥ፣ የጉምሩክ፣ የኢሚግሬሽንና የመሳሰሉ የሁለቱን ሀገሮች ሕዝቦች ተጠቃሚ ሊያደርጉ የሚችሉ የትብብር ማዕቀፎችን ለማበጀት በትኩረት እየተሰራ ነው ተብሏል፡፡

ይህን የገለጹት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸምን ሪፖርት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ያቀረቡ አቶ ደመቀ መኮንን ናቸው፡፡ እየደረሰ ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ጫና በኢትዮጵያ ሕዝብ ጽናት፣ በዳያስፖራው ተሳትፎ እና በኢትዮጵያ ወዳጆች ትብብር መቋቋም መቻሉን አመላክተዋል፡፡

በፍሬህይወት ታደሰ
2022-05-17