የሚወገዱ ንብረቶችን የማያስወግዱ መሥሪያ ቤቶች በጀታቸው ይቀነሳል ተባለ፡፡
የቤተ መንግሥት አስተዳደርን ጨምሮ የፌዴራል መሥሪያ ቤቶች ማስወገድ ያለባቸውን ንብረት እስከ ቀጣዩ አንድ ወር ካላስወገዱ በጀት እስከመቀነስ የሚያስችል እርምጃ በገንዘብ ሚኒስቴር በኩል ሊወሰድ እንደሚችል የመንግሥት ግዥና ንብረት ባለሥልጣን አስታውቋል፡፡
ባለፉት ዘጠኝ ወራት መወገድ የነበረባቸው አገልግሎት የማይሰጡ ከ280 ያላነሱ የቆሙ ተሽከርካሪዎች እና የተለያዩ ቁርጥራጭ ብረቶች መኖራቸውን ማረጋገጥ እንደተቻለ የመንግሥት ግዥና ንብረት ባለሥልጣን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ሰጠኝ ገላን ተናግረዋል፡፡
በፍሬህይወት ታደሰ
2022-05-17
