ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ ንግዱን ለማቀላጠፍ ከሀገር ውስጥ ባንኮች እና የልማት ተቋማት 2 ቢሊዮን ዶላር እፈልጋለሁ አለ፡፡
በኬንያ ትልቁ የሆነው የቴሌኮሙኒኬሽን ኩባንያው በሚቀጥሉት ሰባት ወራት ውስጥ በኢትዮጵያ ቅርንጫፍ የንግድ እንቅስቃሴ ለመጀመር ከሀገር ውስጥ ባንኮች እና የልማት ተቋማት እስከ 2 ቢሊዮን ዶላር የሚደርስ ገንዘብ ነው የጠየቀው፡፡
ሳፋሪኮም የፈቃድ ክፍያን ጨምሮ 540 ሚሊዮን ዶላር በኢትዮጵያ ኢንቨስት አድርጓል ሲል ዘ ኢስት አፍሪካ ዘግቧል፡፡
ተቋሙ በሀገሪቱ የቴሌኮም አገልግሎት ለመስጠት ከኢትዮጵያ መንግሥት በሐምሌ 6/ 2021 ይሁንታ ማግኘቱ አይዘነጋም፡፡
በኢትዮጵያ በነበረው የሰሜኑ ክፍል ጦርነት ሳቢያ ከዓለም ዓቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን ጋር የተደረገው ውይይት መቆሙን ያስታወሰው ሳፋሪኮም አሁን እንደገና ውይይቱ መጀመሩ ተስፋ ሰጥቶታል፡፡
በመቅደስ እንዳለ
2022-05-17
