የዋጋ ንረት እያየለ በመምጣቱ ግብፅ ቁልፍ የምትላቸውን የመንግሥት ኩባንያዎች ወደ ግል ልታዞር ነው፡፡
የግብፅ ጠቅላይ ሚኒስትር ሙስጠፋ ማድቡሊ ሀገሪቱ በፈረንጆቹ ሚያዚያ ወር 15 በመቶ ገደማ የዋጋ ንረት አስመዝግባለች ብለዋል፡፡
በመንግሥት ይፋ የተደረገው ስትራቴጂ 10 የመንግሥት ኩባንያዎችን ወደ ግል ማዞርን ያካትታል ተብሏል፡፡
ግብጽ 160 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋው የሀገሪቱ በጀት ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት 90 በመቶ የሚደርስ የሕዝብ ዕዳ የተሸከመ በመሆኑ ከዓለም ዓቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ጋር ስለ አዲስ ብድር እያወጋች ነው ሲል አፍሪካ ኒውስ አስነብቧል፡፡
በመቅደስ እንዳለ
2022-05-17
