በኢትዮጵያ በየዓመቱ ከሲጋራ ማጨስ ጋር በተገናኘ የ17 ሺሕ ሰዎች ሞት ይመዘገባል። በኢትዮጵያ ከ15 ዓመት የእድሜ ክልል አንስቶ የትምባሆ ተጠቃሚዎች ቁጥር እየጨመረ እንደመጣ መረጃዎች ያሳያሉ። ከአጠቃላይ የኢትዮጵያ ህዝብ ቁጥር ውስጥ ከ15 እስከ 64 የእድሜ ክልል የሚገኙ ዜጎች የትምባሆ ተጠቃሚ በመሆን ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛሉ ሲል የኢትዮጵያ ምግብና መድሃኒት ክብካቤ ባለስልጣን አስታውቋል። በአሁኑ ግዜ የትምባሆ ተጠቃሚዎች ቁጥር ከ3.4 ሚሊዮን በላይ ሲያልፍ ይህም ከአጠቃላይ ሕዝብ ውስጥ 5 በመቶ ድርሻን ይይዛል። ከእነዚህ አጫሾች ውስጥ የአፋር ክልል 15 ከመቶውን በመውሰድ ቀዳሚ ሲሆን ጋምቤላ በ11.2 በመቶ ሁለተኛውን እንዲሁም ሀረር ደግሞ በ7.2 በመያዝ ሦስተኛ ደረጃ ላይ ይቀመጣሉ። ከአጠቃላይ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ውስጥ 2.2 በመቶዎቹ ሲጋራ አጫሾች መሆናቸውን ጥናት ተመላክቷል። በዓለም ዓቀፍ ደረጃ 8 ሚሊዮን ገደማ ሰዎች ከሲጋራ ጋር በተገናኘ ለሞት ሲዳረጉ፤ 1 ሚሊዮን የሚሆኑት ባያጨሱም አጠገባቸው ባሉ አጫሾች ምክንያት ለህልፈት የሚዳረጉ ናቸው።
በሀገሬ ቲቪ
2021-12-08
