የሞት የምስክር ወረቀቶች እንደሚያሳዩት ኮቪድ 19 አሜሪካን ላይ አስከፊ በትሩን አሳርፏል፡፡
1 ሚሊዮን አሜሪካውያን በኮቪድ-19 ምክንያት ለሞት እንደተዳረጉ የሀገሪቱ መንግሥት ተናግሯል፡፡
የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማእከል ሲዲሲ ከአሜሪካ 50 ግዛቶች መረጃ በመሰብሰብ በመንግስት ይፋ የሆነውን መረጃ አረጋግጧል፡፡
ነገር ግን ብሏል ሲዲስ በወረርሽኙ የመጀመሪያ ወራት ላይ የሀገሪቱ ሹማምንት በሽታውን የተመለከተ መረጃን በማደራጀቱ ደካማ በመሆናቸው ተወቃሽ ናቸው፡፡
ጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ በግንባር ቀደምትነት የጤና ድረ-ገጾችን በመፈለግ እና ቁጥሮቹን በፍጥነት በመተንተን መረጃውን በማጠናቀር ሂደት ውስጥ ከሲዲሲ ጋር እጅና ጓንት ሆኖ ሰርቷል፡፡
በመቅደስ እንዳለ
2022-05-17
