ሀገሬ ቲቪ

ኑሮን አቅላዩ ቴክኖሎጂ

በሀገሪቱ ቤት መሸጥ፣ መለወጥ አልያም ማከራየት እንዲሁ በቀላሉ የሚደረግ አይደለም። ከላይ ወደ ታች መባዘንና አገናኝ ኤጀንሲዎች ጋር ደጅ መጥናት የተለመደ ሆኗል። ይህ በቤት ዙሪያ የሚደረግ መኳተንን ለማስቀረት ቴክኖሎጂ ቀመስ የሆነ አሰራርን ይዤ መጥቻለሁ ብሏል እፎይ ፕላስ ።

ድርጅቱ አፎይ ፕላስ ዶት ኮም በተሰኘ ድህረ ገጽ የሚከራይና የሚሸጥ ቤት ፣ የግንባታና የኮንስትራክሽን ቁሳቁስ መሽጥና መግዛት ይቻላል ተብሏል ። በተጨማሪም በዚሁ ለባንኮች ድህረ ገጽ ለጨረታ የቀረቡ ቤቶችን በቀላሉ ማግኘትና መግዛት እንደሚቻል የእፎይ ፕላስ ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ጌትነት ዘመነ ተናግረዋል።

በሀገሪቱ ያለው የቤት አቅርቦትና ፍላጎት አጅጉን የተራራቀና ያልተመጣጠነ ነው ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚው በቤት ግዢና ሽያጭ ገበያ ላይ ወጥ የሆነ የመረጃ ሥርዓት አልመኖርና ተያያዥ ችግሮች እፎይ ፕላስ ድህረ ገጽ እንዲፈጠር ምክንያት ሆኗል ብለዋል።

ድርጅቱ ባደረገው ጥናት ለቤት ሽያጭና ግዢ በዓመት 400 ቢሊዮን የገንዘብ ዝውውር ይደርግበታል። ይህ ከፍተኛ የንግዱ ዘረፍ ግን በሚመጥነው ልክ በቴክኖሎጂ ባለመደገፍ ቤት መሸጥም ሆነ መግዛት ራስ ምታት መሆኑ ተገልጿል። በድህረ ገጽ ማንኛውም ቤት መሸጥ ሆነ መግዛት የሚቻልበትን መንገድ ያመቻቸው አፎይ ፕላስ ከሌላው መሰል አሰራሮች የሚለየን ከአገልግሎት ክፍያ ውጪ ኮሚሽን አለመቀበላችን ነው ብሏል። በዚህም ግዢና ሻጭ እስከ 200ሺሕ ብር ከግብይት የሚያተርፉበት ነው ሲሉ አቶ ጌትነት ተናግረዋል።

አፎይ ፕላስ በዚሁ ዘርፍ የሚሰሩ ብሮከሮችን በተለምዶ “ደላላ” የሚባሉትን ወደ ተቋሙ በማምጣትና ስልጠና በመስጠት አንድ ላይ የመስራት ዕቅድና ፍላጎት እንዳለው ተናግሯል። በዚህም እስከ 2 መቶ ለሚደርሱ ዜጎች በቀላሉ ቤት መሸጥ በፈለጉት ቦታ መግዛት እንደሚችሉ እፎይ ፕላስ አስታውቋል።

በሙሉጌታ በላይ
2022-05-17