ሀገሬ ቲቪ

የመንግስት ውሳኔ በዘይት ላይ

በሚቀጥሉት ሶስት ወራት 150 ሚሊዮን ሊትር የምግብ ዘይት ከውጭ ይገባል ተባለ፡፡አሁን ላይ 12 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሊትር የምግብ ዘይት ወደ ሀገር ውስጥ እየገባ መሆኑን የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ ተናገረዋል። ከዚህ ውስጥ 4 ነጥብ 8 ሚሊዮን ሊትር ዘይት ወደ ሀገር ውስጥ ገብቶ ለኅብረተሰቡ እየተከፋፋለ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ቀሪው 7 ነጥብ 7 ሚሊዮን ሊትር ዘይት ደግሞ በሚቀጥሉት ሶስት ሳምንታት ውስጥ ወደ ሀገር ውስጥ እንደሚገባ ሚኒስትሩ አስረድተዋል፡ባለፉት ሁለትና ሶስት አመታት የምግብ ዘይት ከቀረጥ ነጻ እንዲገባ በመደረጉ 23 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ታጧል ብለዋል።ለነዳጅ የ100 ቢሊዮን ብር ድጎማ ማድረጉን መናገራቸውን የገንዘብ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

በመቅደስ እንዳለ
2022-05-18