ሕዝቡን ወደ እርቅና ወደ ይቅርታ ማምጣት የሃይማኖት አባቶች ቀዳሚ ተግባር ነው ተባለ፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የ2014 የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባዔ የመክፈቻ መርሃግብር ዛሬ ተከናውኖል፡፡ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በጉባኤው መክፈቻ ላይ እንደገለጹት የእርቅን ጥቅም በመቀበል ወደ ተሻለ ነገር መራመድ ጊዜው የሚጠይቀው ተግባር መሆኑን አስታውሰዋል፡፡
ሕዝቡን ወደ እርቅና ወደ ይቅርታ ማምጣት የሃይማኖት አባቶች ቀዳሚ ተግባር ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡በተጨማሪም ቅዱስ ጉባዔው ለሁሉም ኢትዮጵያውያን ሰላም መሥራትና መጣር ይጠበቅበታል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡የግንቦቱ የርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በጠዋቱ መርሐ ግብር ለጉባኤው አጀንዳ የሚያረቁ 7 ብፁዓን አባቶችን የያዘ ኮሚቴ ሰይሟል፡፡
በፍሬህይወት ታደሰ
2022-05-18
