ከሮኬት ሞተር የሚወጣው ጭስ ወደ ምድር ከባቢ አየር እየዘለቀ ነው ተባለ። በስፔስ ትራንስፖርቱ ዘርፍ ስፔስ ኤክስ እና ቨርጂን ጋላክቲክ የተባሉት ኩባንያዎች ሰዎችን ወይም ጭነቶችን ወደ ጠፈር ለማጓጓዝ ዝቅተኛ ክፍያን በመጠየቅ ተመራጭ ቢሆንም ከባቢን እየጎዱ በመሆኑ ወቀሳ እያስተናገዱ ነው። በዚህም በከባቢ አየር ውስጥ ከፍተኛ ሙቀት በመፈጠር ላይ መሆኑን ዴሊ ኒውስ ጽፏል። በቆጵሮስ የኒኮሲያ ዩኒቨርስቲ የፊዚክስ ተመራማሪዎች በሮኬቶች ሳቢያ የሚመጡ የከባቢ ብክለቶች እንደ ቀልድ መታየት የለባቸውም ብለዋል። እንደ ጠበብቶቹ ወደ ፊት በምድር የአየር ንብረት ላይ ከፍተኛ የሆነ ተጸእኖ ይጠበቃል። ተመራማሪዎቹ በመርዛማ ጋዝነት የሚታወቀውን ናይትሮጅን ኦክሳይድን በከባቢው ውስጥ ማገኘታቸውን ተናግረዋል።
በመቅደስ እንዳለ
2022-05-18
