ዚምባቡዬ የደርግ ሊቀመንበር የነበሩትን ኮሎኔል መንግሥቱ ኃ/ማርያምን የኢትዮጵያ መንግሥት የሚፈልጋቸው ከሆነና ከተጠየኩ ለመተባበር ፈቃደኛ ነኝ አለች።
የዚምባብዌ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ፍሬድሪክ ሻቫ እንደተናገሩት ከሆነ ሀራሬ በዘር ማጥፋት ወንጀል የተከሰሱትን የቀድሞ ፕሬዝዳንት መንግስቱ ኃ/ማርያምን ከተጠየቀች ለመስጠት ዝግጁ መሆናን ግልጽ ፍንጭ አሳይተዋል ተብሏል።
ሻቫ ከቪኦኤ ጋር ባደረገው ልዩ ቃለ ምልልስ ከኢትዮጵያ መንግሥት ሆነ ሕዝብ ሕጋዊ ጥያቄ ከቀረበልን የዚምባቡዌ መንግሥት አስፈላጊውን ትብብር ያደርጋል ብለዋል።
‘‘መንግሥቱ ኃ/ማርያምን ከሕዝቡ ሸሽቶ ከመጣ ወዲህ በሀገራችን እንዲኖር ፈቀድን እንጂ እንዲሸሸግ አላደረግንም፤ ከቤተሰቡ ጋር ወደዚህ እንደመጣ ሁሉም የሚያውቀው ነው፤ይህ ሴራ አልነበረም’’ ሲሉ አምባሳደር ፍሬድሪክ ሻቫ ተናግረዋል።
በፈረንጆቹ 2009 የቀድሞ የዚንባቡዬ ኢንፎርሜሽን ሚንስቴር ሀራሬ ኮሎኔል መንግሥቱ ኃ/ማርያምን አሳልፋ እንደማት ሰጥ አረጋግጠው ነበር። አሁን ላይ ታዲያ የኢትዮጵያ መንግሥት የሚፈልጋቸው ከሆነ ለመተባበር ፍንጭ መስጠቷ የፖሊሲ ለውጥን ያሳያል ሲል ቪኦኤ ዚሙባብዌ አስነብቧል።
መንግስቱ ኃ/ማርያም 1883 ከሥልጣን ከተወገዱ በኋላ ወደ ዚምባብዌ ሔደዋል። ግንቦት 18 ቀን 2000 ዓ.ም. በፌድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በዋለው ችሎት ኮሎኔል መንግሥቱ መንግስቱ በዘር ማጥፋት፣ በነፍስ ማጥፋት፣ በሕገወጥ እስራት እና በንብረት መውረስ ከሌሎች 20 ባልደረቦቻቸው ጋረ በሌሉበት በሞት እንዲቀጡ ተፈርዶባቸው እንደነበር ይታወሳል።
በጉዳዩ ላይ የኢትዮጵያ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴርን ለማናገር ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።
በሙሉጌታ በላይ
2022-05-19
