ሀገሬ ቲቪ

‹‹የመጨረሻው ከባድ ስህተት››

ጦርነቱ ዛሬ ነገ ያበቃል ከስምምነት ይደረሳል ቢባልም እየተባባሰ እየተፋፋመ መጥቷል፡፡

ለሩሲያና ለዩክሬን ጦርነት መነሳት ዋነኛ ምክንያት የተባለው የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶን) ዩክሬን እቀላቀላለሁ ማለት እና ሩሲያ ግድ የለም ይሄ ያጣላናል ብትልም ሰሚ ማጣት በከፍተኛ ደረጃ ውጥረቱን አካሮ ወደ ጦርነት አምርቷል፡፡

ከዩክሬን ያልተማሩት እንደ ስዊድን እና ፊንላንድ ያሉ ሀገራት ስዊድን እና ፊንላንድ የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶን) የመቀላቀል ጥያቄን ይፋ ማድረጋቸው አይረሳም፡፡

ኔቶም የዚህን ጥያቄ መመለሻው ሰዓት አሁን አይደለም በሚል ያዘገያል ቢባልም ውጥረቱ እየተካረረም ቢሆን ትላንት ምሽት የሁለቱን ሀገራት ጥያቄ መቀበሉ አነጋጋሪ ሆኖል፡፡

አፍተንብላዴት የተባለ የስዊድን ጋዜጣ ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ እንደጻፈው ሁለቱ ሀገራት ኔቶን ለመቀላቀል በሚያቀርቡት ማመልከቻ ላይ አሜሪካ እና ዩናይትድ ኪንግደም ድጋፍ እንደሰጦቸው የስዊድን መንግሥት ባለስልጣናትን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል፡፡

ስቶኮልም እና ሄልሲንኪ በቀጠናው ካሉ ሀገራት ጋር ወታደራዊ ግጭት ውስጥ ላለመግባት ሲሉ እራሳቸውን ከወታደራዊ እንቅስቃሴዎች አቅበው ቢቆዩም ሩሲያ ዩክሬን ላይ ጥቃት ከከፈተች በኋላ ደብዳቤያቸውን በማስገባት ተቀባይነት አግኝተዋል፡፡

ደብዳቤዎቹ በኔቶ የፊንላንድ አምባሳደር ክላውስ ኮርሆኔን እና በኔቶ የስዊድን አምባሳደር አክሴል ቨርንሆፍ ለኔቶ ዋና ፀሃፊ ጄንስ ስቶልተንበርግ በብራሰልስ ዋና መሥሪያ ቤት ተቀብለዋል፡፡ ሚስተር ስቶልተንበርግ ይህንን ብለዋል፡፡

“እንኳን ደህና መጣችሁ ፊላንድ እና ሲዊድን ኒቶን ስለተቀላቀላችሁ ደስ ብሎናል፡፡ እናንተ የቅርብ አጋሮቻችን ናችሁ፡፡ ይህ ጥሩ ቀን ነው፣ ለደህንነታችን ወሳኝ ወቅት ነው ጥያቄያችሁን በደስታ ተቀብለነዋል” ብለዋል፡፡

ከስዊድን ጋር ድንበር የምተጋራው ቱርክ ለብሔራዊ ጥቅም እንዴት መዋጋት እንዳለባት እያሳየች ነው፤ ስዊድን እና ፊንላንድን አሸባሪዎችን እና አጋሮቻቸውን ሳያወግዙ ኔቶ ደብዳቤውን መቀበሉ አጥብቃ ተቃውማለች፡፡

ዛሬ በወጣ መረጃ የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በበኩላቸው ይህ ታሪካዊ ቀን ነው በማለት የሁለቱን ሀገራት ወደ ኔቶ መቀላቀል በጽኑ ደግፈዋል፡፡

“ወደ ፊንላንዱ ፕሬዝዳንት ደውዬ ስላለው ሁኔታ ተነጋግረናል፤ የሁለቱም ሀገራት መሪዎች ጋር ሀሙስ ደውያለሁ ደህና እንሆናለን ብዬም አስባለሁ” ብለዋል፡፡

ፊንላንድ ከሩሲያ ጋር ረዥም ድንበር የምትጋራ በመሆኖ የኔቶን መቀላቀል ከሞስኮ ጋር ውጥረት ውስጥ ከአሁኑ ከቷታል፡፡ ሩሲያ ከጅምሩ የሁለቱ ሀገራት ኔቶን መቀላቀል ትርፉ በአውሮፓ አለመረጋጋትን መፍጠር ነው በሚል እንዲቆጠቡ አሳሰበች፡፡

‹‹ሩሲያ ፊንላንድ እና ስዊድን ኔቶ ሲቀላቀሉ ዝም አትልም›› ሲሉ የሀገሪቱ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ሪያብኮቭ ሰኞ አስጠንቅቀዋል፡፡ እንዲህ ያለው እርምጃ ደኅንነታቸውን ከማጠናከር ይልቅ ደህንነታቸውን እንደሚጎዳ ተጠቁሟል፡፡

ባለሥልጣኑ ከሩሲያ ጋዜጠኞች ጋር ባደረጉት ቆይታ የሁለቱ ሀገራት እርምጃ በምዕራቡ ዓለም “የመጨረሻው ከባድ ስህተት ለረጅም ጊዜ የሚቆዩ ችግሮች” በማለት የገለጹ ሲሆን “ይህ ውሳኔ የሚወስዱትን ሰዎች ደረጃ ያሳያል” ብለዋል፡፡

በዚህ በኩል ያላበቃው የሩሲያና የዩክሬን ጦርነት በወዲህ የፊላንድ እና ሲዊድን ወደ ኔቶ መቀላቀል ሩሲያና ቱርክን ያስቆጣ በሌላ ወገን አሜሪካና እንግሊዝ ብሎም ሌሎች አጋሮቻቸው ያስደሰተው ውሳኔ መጨረሻው የከፋ እንደሚሆን የዓለም የፖለቲካ ተንታኞች እየተናገሩ ነው ፡፡

ቀድሞውንም ማስፈራሪያ የላከችው ሩሲያ በፊንላንድ ላይ ጉጊያ ትጀምራለች የሚል ስጋትም እንዳለ አስቀምጠዋል፡፡ መቀመጫውን ቤልጄም ብራሰልስ ያደረገው ተቋሙ አሁን ላይ 34ኛ የኖርዌይ ጠቅላይ ሚኒስትር በነበሩት ጀንስ ስቶልተንበርግ እየተመራ ይገኛል፡፡

ስዊድን እና ፊንላንድ ትላንትንት ማምሻውን ወደ ኔቶ መቀላለቀል የሕብረቱ አባላት ቁጥር ወደ 32 ከፍ ሊያደርጉት ይችላሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በፍሬህይወት ታደሰ
2022-05-19