እርሶ አላማዎን ለማሳካት የትኛው ጥግ ድረስ ይጓዛል።
ወደ ህልሞ ለመድረስ ፈተናዎችን ያለተስፋ መቅቁረጥ ማለፍን ይጠይቃል።
እኛም ታዲያ ተስፋ ያለመቁረጥ ምሳሌ የሚሆነን አንድ ግለሰብ ልናስተዋውቃችሁ ወደናል።
ኮሌጅ መግባትን የህልሙ ጥግ ያደረገ የ55 ዓመት ቻይናዊ አሁንም ሳይሰለች የኮሌጅ መግቢያ ፈተናዎችን እየወሰደ ነው።
ቻይናዊው ጎልማሳ ለ25 ግዜያት የኮሌጅ መግቢያ ፈተናዎችን ቢወስድም ማለፍ ሳይችል ቀርቷል።
የ55 ዓመቱ ሊያንግ ሺ በደቡብ ምዕራብ ቻይና የሲቹዋን ግዛት ዋና ከተማ በሆነችው በቼንግዱ የተሳካለት የግንባታ ቁሳቁስ አቅራቢ ኩባንያ ባለቤት ነው።
የሚፈልገውን ማድረግ የሚያስችል የተትረፈረፈ ሀብት ባለቤት የሆነው ቻይናዊ ህልሜ ግን ሙሉ አይደለም እያለ ነው።
ነብስ ካወቀ ጀምሮ ወደ ሲቹዋን ዩኒቨርሲቲ የመግባት ህልም እንደነበረው ይናገራል።
ሊያንግ ሺ ታዲያ አብዛኛው ሰው ከስራ ጡረታ ስለመውጣት በሚያስበብት እድሜ የጋኦካኦ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና አልፎ ዲግሪ ስለመያዝ እያለመ ይገኛል።
ባለ ትልቅ ህልሙ ቻይናዊ ላለፉት 25 ግዜያት የዩኒቨርሲቲውን መግቢያ ፈተና ቢወስድም ሳይሳካለት ቀርቷል።
አሁንም ግን ተስፋ አልቆረጠም ለ26ተኛ ግዜ ለመፈተን እራሱን እያዘጋጀ ይገኛል።
ሺ ሲናገር እንዲህ ይላል፤ አሁን 55 ዓመቴ ላይ እገኛለው ለመማር ገና ነኝ። እስካሁን ታሪክን እና ጂኦግራፊን ለመማር ፍላጎት አለኝ፤ ወደ ምወደው ትምህርት ቤት ለመግባት የመግቢያ ፈተናውን ማለፍ አለብኝ፣ ስለዚህ ህልሜን እውን እስከማደርግ ድረስ ሙከራዬን አላቆምም። ሲል።
እንደ ምዕራባውያኑ ከ1983 ጀምሮ የመግቢያ ፈተናውን እየወሰደ ይገኛል።
ከ83 ጀምሮ ለ14 ግዜያት በተከታታይ የመግቢያ ፈተናዎቹን ወስዷል።
በመሀል በሀገሪቱ የመጡ የፖሊሲ ለውጦች ሙከራውን እንዳይቀጥል እንቅፋት ሆነውበት ነበር።
ቻይና ወደ ዩንቨርሲቲ ለመግባት ትዳር አለመያዝን እና ከ25 ዓመት በታች መሆንን እንደ መስፈርት ታስቀምጥ ነበር።
ሺ እስካሁን ከወሰዳቸው 25 የሚደርሱ ፈተናዎች ምርጥ ነጥብ ከ750 ውስጥ 400 ነጥብ ነው።
ይህ ነጥብ ታዲያ ወደሌሎች ዩንቨርሲቲዎች ውስጥ ለመግባት ቢያስችለውም እሱ ግን የሺ ህልም አይደለም።
ወደ ሲቹዋን ዩኒቨርሲቲ ለመግባት የሚያስችለውን ነጥብ ለማምጣት ለ26ተኛ ግዜ ሙከራውን እንደሚቀጥል ተናግሯል።
ጋኦካዎ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ተማሪዎች በቻይና ከፍተኛ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ለመግባት ፈተናዎችን የሚወስዱት በዓለም ላይ ካሉ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተናዎች በጣም ከባዱ ተደርጎ ይቆጠራል።
ሊያንግ ሺይህንን ከባድ ፈተና ተሻግሮ ወደህልሙ ዓለም ለማቅናት ለ26 ተኛ ግዜ መንገዱን ጀምሮታል።
በሳምሶን ገድሉ
2022-05-19
