ሀገሬ ቲቪ

የተዘረፉት የኢትዮጵያ ቅርሶች

ፈረንሳይ በሕገ-ወጥ መንገድ ወደ ሀገሯ የገቡ የኢትዮጵያ ቅርሶችን እመልሳለሁ ብላለች።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንደገለጸው ከ15ኛው ክፍለ ዘመን እስከ 20ኛው ክፍለ ዘመን ጅማሮ ባሉት ዓመታት ውስጥ የተሰሩት ቅርሶቹ ከሦስት ዓመታት በፊት በሕገ-ወጥ መንገድ ከኢትዮጵያ ወደ ፈረንሳይ ከተጓጓዙ በኋላ በፓሪስ ሮይሲ አውሮፕላን ማረፊያ የተያዙ ናቸው ተብሏል።

በፈረንሳይ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ከጉምሩክ ባለስልጣን ጋር በጉዳዩ ላይ የተወያየ ሲሆን፤ ቅርሶቹ በመጪው ሰኔ ወር እንደሚመለሱ ተሰምቷል።

ኢትዮጵያና ፈረንሳይ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የጀመሩበትን 125ኛ ዓመት በሚያከብሩበት በዚህ ወቅት፤ የቅርሶቹ መመለስ የኹለቱን ሀገራት በባህል ዘርፍ ያላቸውን ጠንካራ ትስስር አመላካች ነው ተብሏል።

በፍሬህይወት ታደሰ
2022-05-19