ግምታዊ ዋጋው 16 ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ የኤክስፖርት ቡና ሰውረዋል የተባሉ አሽከርካሪዎች ምርመራ እየተደረገባቸው።
የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን እንደገለጸው ተጠርጣሪዎቹ ከቡና የሽኝት ጣቢያዎች የወሰዱትን ቡና ወደ ኤክስፖርት ማዘጋጃና ማከማቻ ሳያደርሱ ተሰውረዋል።
ይሁን እንጂ ቡናው ተጭኖባቸው የነበሩ 18 ተሽከርካሪዎች ተይዘዋል።
በግለሰቦቹ የተሰወረው ቡና 77.7 ቶን ቡና ሲሆን ሀገሪቱ ወደ ውጪ ልካ ልታገኝ የነበረውን የውጭ ምንዛሪ የሚያሰናክል ተግባር ፈጽመዋል ተብሏል።
በፍሬህይወት ታደሰ
2022-05-19
