ሀገሬ ቲቪ

አሳሳቢው ቫይረስ

በሞዛምቢክ ከሶስት አስርት አመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ዋይልድ ፖሊዮ ቫይረስ መገኘቱን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ።

ቫይረሱ በቅርቡ የሞዛቢክ ጎረቤት በሆነችው ማላዊ የታየ ቢሆንም በሌላ የ አፍሪካ ሀገር ድጋሜ መታየቱ አሳሳቢ ነው ተብሏል። አዲሱ ዋይልድ ፖሊዮ የጀርባ አጥንትን የሚያጠቃ እና አካላት እንዳይንቀሳቀሱ የሚያደርግ ሲሆን በፍጥነት ተላላፊ መሆኑ አስከፊ ያደርገዋል።

በዚህም ምክንያት ማላዊ ፣ ሞዛምቢክ፣ ታንዛኒያ፣ ዛምቢያ እና ዚምባብዌ - ከአምስት አመት በታች የሆኑ 23 ሚሊዮን ህጻናትን ለመከተብ አቅደዋል።

በዮሴፍ ከበደ
2022-05-19