አፍሪካ ለዓለም የምታቀርበውን የነዳጅ ምርት ማሳደግ እንዳለባት ተገለጸ።
የአፍሪካ ዋና ዋና የነዳጅ ዘይት አምራቾች እና ላኪዎች በአንጎላ ዋና ከተማ ሉዋንዳ እየመከሩ ይገኛሉ።
ምዕራባውያኑ ከሩሲያ ጋር በገቡበት ፍጥጫ ሳቢያ የሀይል ፍላጎታቸውን ለማሟላት መስፈርቶቻቸውን ትተው አፍሪካን ማማተር መጀመራቸው አዲስ እድልን ይዞ መጥቷልም ነው የተባለው።
አፍሪካ ያላትን የነዳጅ ምርት በተሻለ ደረጃ ለማቅረብ ተጨማሪ ኢንቨስትመንቶችን በዘርፉ ላይ ማድረግ እንደሚገባትም ተተቁሟል።
ሳምሶን ገድሉ
በሳምሶን ገድሉ
2022-05-19
