ሀገሬ ቲቪ

የኮሜዲያን ዶክሌ ህልፈት

ኮሜዲያን ወንድወሰን ብርሃኑ ወይም በተለምዶ ስሙ ዶክሌ በተወለደ በ57 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

ኮሜዲያኑ ባጋጠመው የልብ ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ትናንት በሀገረ አሜሪካ ዋሽንግተን ማረፉን አርቲስት ቴዎድሮስ ለገሰ ገልጿል። አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ተወልዶ ያደገው ኮሜዲያን ዶክሌ በመድሐኒአለም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ትምህርቱን ተከታትሏል።

በመካኒክነት ስራ ሲሰራ የቆየ ሲሆን ኋላ ላይም ወደ ጥበቡ በመሳቡ በኮሜዲ ዘርፍ ተወዳጅነትን ያስገኙለትን ሥራዎችን ሰርቷል። በስታንድ አፕ ኮሜዲ በርካታ አጫጭር ቁምነገር አዘል ቀልዶችን ያቀረበው ኮሜዲያን ዶክሌ የፊልም ሥራዎች ላይ በመሳተፍም ዕውቅናን አትርፏል። ኮሜዲያን ወንድወሰን ብርሃኑ ባለትዳርና የአምስት ልጆች አባት ነበር።

በመቅደስ እንዳለ
2022-05-20