የገቢዎች ሚኒስቴር ባለፉት 10 ወራት 82 ቢሊዮን ብር ዋጋ ያላቸው እቃዎች ከቀረጥ ነጻ ገብተዋል አለ።
የገቢዎች ሚኒስትር ላቀ አያሌው የተቋሙን የ10 ወራት ሪፖርት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርበዋል።
ቀደም ሲል በክልሎች መሥሪያ ቤቱ ይሰጥ የነበረው የቀረጥ ነጻ መብት በአሁኑ ወቅት በአንድ ማዕከል በገንዘብ ሚኒስቴር በኩል እንደተደረገም ተነግሯል።
የጉምሩክ ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ በበኩላቸው የቀረጥና ታክስ ነጻ መብት በልዩ ሁኔታ ኢንቨስትመንትን ለማበረታታትና የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።
በዚህም ባለፉት 10 ወራት የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት መንግሥት 38 ቢሊየን ብር ከቀረጥ ነጻ መፍቀዱን ጠቁመዋል።
በመቅደስ እንዳለ
2022-05-20
