በፈረንጆቹ 2021 በዓለም ዙሪያ ወደ 60 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ተፈናቅለዋል ተባለ።
ምዕራብዉያኑ አምና ባሉት ዓመት በተከሰቱት ግጭቶች እና የተፈጥሮ አደጋዎች ሰዎች ወደ ሀገራቸው እንዲሰደዱ ያስገደዳቸው ሲሆን ይህም የተፈናቀሉ ዜጎችን ቁጥር ወደ ከፍተኛ ደረጃ ከፍ እንዲል አድርጎታል ሲል ሲጂቲኤን ጽፏል።
አሁን ደግሞ በጦርነት በምትናጠው ዩክሬን ውስጥ ከፍተኛ መፈናቀል እንዳይከሰት ተፈርቷል።
የሀገር ውስጥ መፈናቀል ክትትል ማእከል (IDMC) እና የኖርዌይ የስደተኞች ምክር ቤት (ኤንአርሲ) በጋራ እጥንተው ነው ይህን መረጃ እንካችሁ ያሉት።
እንደ ጥናቱ ከቀደሙት አመታት ጋር ሲነጻጽር በ 14.4 ሚሊዮን ከፍ ብሏል ነው የተባለው
በመቅደስ እንዳለ
2022-05-20
