የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በዓለም መከሰትን ተከትሎ ከ15 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ህይወታቸው አልፏል። የተያዘው፣ የታመመው፣የተሰቃየው የደረሰበት ህመሙን ያውቀዋል።
የሀገራት የኑሮ ዘይቤ መቀየር በርካቶችን ለረሃብ መዳረግ የምጣኔ ሃብት ድቀት እና መሰለል መዘዞቹም ዛሬም አልቀሩም።
የኮቪድን እፎይ ብለን ሳናበቃ መነሻውን በመካከለኛውና ምዕራብ አፍሪካ ያደረገ አንድ ቫይረስ በአፋጣኝ እየተሰራጨ መሆኑን ሰማን።
የዓለም የጤና ድርጅት (ደብሊው ኤች ኦ) ጉዳዩ ከተሰማበት ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በእንግሊዝ፣ በፈረንሳይ፣ በጀርመን፣ በቤልጂየም፣ በጣሊያን፣ በፖርቹጋል፣ በስፔን ፤ በስዊድን ፣ በአሜሪካ፣ በካናዳ ፣ በአውስትራሊያ፣ እስራኤል እና ስዊዘርላንድ የጦጣ ፈንጣጣ በሽታ(Monkeypox) መገኘቱን ተከትሎ ቫይረሱ ሊስፋፋ ይችላል የሚል ስጋት እንዳለው ገልጿል።
በሽታው የሚከሰው መንኪፖክስ በተባለ ቫይረስ ነው ይላሉ የጤና ባለሙያዎች ለፈንጣጣ (ስሞልፖክስ) ከሚያጋልጠው ቫይረስ ጋር ዝርያው ይቀራረባል። የጦጣ ፈንጣጣ ቫይረስ ከፈንጣጣ ጋር ሲነጻጸር የሚሰራጭበት ፍጥነት አናሳ ከመሆኑም በላይ ሕመሙም ብዙም አይበረታም ይላሉ።
በእንግሊዝ ውስጥ ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች ሁለቱ ከናይጄርያ የተጓዙ ናቸው ተብሏል፤ ስለዚህ የተገኘባቸው ከምዕራብ አፍሪካው ቫይረስ ሊሆን የሚችልበት ዕድል ሰፊ ነው።
ሳይንቲስቶች እንደሚሉት ቫይረሱ በሌለባቸው ሀገሮች ውስጥ ያለው ወረርሽኝ ያልተለመደ እንዲሁም የአሁኑ የጦጣ ፈንጣጣ (Monkeypox) ዝርያ የሚለየዉ በግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚተላለፉ ኢንፌክሽኖች ሊሆን እንደሚችል እየተገለፀ ይገኛል።
ጂሚ ዊዝወርዝ በለንደን የተላላፊ በሽታዎች ትምህርት ክፍል ኃላፊ ናቸው።
“በሽታውን እንደተመለከትነው የተጠቁ ሰዎች ወደ አውሮፓ ሀገራት የገቡ የምዕራብ አፍሪካ የጉዞ ታሪክ ያላቸው ናቸው ስለዚህ ከዛእንደመጣ ማሳያ ነው ። እንደ ኮሮና ቫይረስ ሕብረተሰቡ ጋር በቀላሉ አይሰራጭም የሚል እምነት አለን እናም ሰፊውንም ሕዝብም አያጠቃም። ብለዋል።
የዓለም ጤና ድርጅት በበሽታው ከተጠቁ ሀገራት እና ከሌሎች ጋር በመሆን የበሽታ ክትትልን በማስፋት የተጠቁ ሰዎችን ለማግኘት እና ለመደገፍ እንዲሁም በሽታውን እንዴት መቆጣጠር እንደሚቻል መመሪያ ለመስጠት እየሰራ እንደሆነ ገልጿል።
የጦጣ በሽታ ከኮቪድ-19 በተለየ ሁኔታ ይተላለፋል ይላሉ ፤ሆኖም ግን በንክኪ ከሰዉ ወደ ሰዉ ሊተላለፍ ስለሚችል ጥንቃቄ ባይለይ ይመክራሉ።
ሰዎች ብዙውን ጊዜ ከሁለት እስከ አራት ሳምንታት ውስጥ ሆስፒታል መተኛት ሳያስፈልጋቸው ይድናሉ ነገር ግን በሽታው አልፎ አልፎ እስከ መግደል ይደርሳል።
የዓለም ጤና ድርጅት ባለስልጣን እና የተላላፊ በሽታ ባለሙያ የሆኑት ዴቪድ ሄይማን እንደገለጹት
‹‹አሁን እየተፈጠረ ያለ የሚመስለው በሕዝቡ ውስጥ በግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚተላለፉኢንፌክሽኖች እየተሰራጩ ነው፣ ይህም በመላው ዓለም ስርጭቱን አባብሶታል ብለዋል››።
የበሽታው ዓይነተኛ ቁስሎች በጣም ተላላፊ በመሆናቸው የቅርብ ግንኙነት ዋናው የመተላለፊያ መስመር ነው ብለዋል።ለምሳሌ የታመሙ ሕፃናትን የሚንከባከቡ ወላጆች፣ የጤና ባለሙያዎችም አደጋ ላይ ናቸው።ለዚህም ነው አንዳንድ ሀገሮች የጦጣ ሕመምተኞች ተዛማጅ ቫይረስ ክትባቶችን በመጠቀም የዝንጀሮ በሽታዎችን የሚያክሙ ቡድኖችን መከተብ የጀመሩት።
በዩናይትድ ኪንግደም የጤና ጥበቃ ኤጀንሲ አርብ ዕለት 20 ተያዞችከተመዘገቡ በኋላ አዲስ አሃዞች ዛሬ ይፋ እንደሚሆኑ ገልጿል።
በዩናይትድ ኪንግደም የጤና ጥበቃ ዋና የህክምና አማካሪ ኢሪክ ሾኒ እንዳሉት
“ወረርሽኙ ቀጥታ የመተላለፊያ መንገዱን ስንመለከተው በግብረ ሰዶማውያን ወይም በሁለትወንዶች መካከል በተደረገ ግንኙነትላይ ያተኮረ ነው ይህ ማለት በቅርብ ግንኑነት የተፈጠረ ነው ።ይሄ ማለት በጣም ቅርብ የሆነ የፊት ለፊት ግንኙነት ለበሽታው መዛመድ ምክንያት መሆኑን ማሳያ ነው።”
እንደ የዓለም ጤና ድርጅት ገለፃ በሚቀጥሉት ሳምንታት ከተለያዩ የአዉሮፓ ሀገራት የጦጣ ፈንጣጣ በሽታ ሪፖርት ሊኖር እንደሚችል ከወዲሁ ተገምቷል።
በፍሬህይወት ታደሰ
2022-05-23
