ሀገሬ ቲቪ

በእንስሳት ላይ አደጋ የጋረጠው የቦረና ድርቅ

በቦረና በተከሰተው ድርቅ ብርቅዬ የዱር እንስሳት ለአደጋ ተጋልጠዋል፡፡ በቦረና ዞን በተከሰተው ድርቅ ምክንያት በዞኑ በሚገኘው ቦረና ብሔራዊ ፓርክ የሚገኙ ብርቅዬ የዱር እንስሳት ለአደጋ መጋለጣቸው ተሰምቷል፡፡ በድርቁ ምክንያት በአካባቢው ከፍተኛ የግጦሽና የውኃ እጥረት በመኖሩ እንስሳቱ አደጋ ተደቅኖባቸዋል፡፡ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል የዱር እንስሳት ፓርኮች እና ኢኮቱሪዝም ዳይሬክተር መሐመድ ኑር ጀማል እንደገለጹት በምስራቅ አፍሪካ ኢትዮጵያና ኬንያ ብቻ ከሚገኙ የሜዳ አህያ ዝርያዎች አብዛኞቹ በቦረና ብሔራዊ ፓርክ እንደሚገኙ ጠቁመዋል፡፡ አሁን ላይ በዞኑ ባለው ድርቅ ምክንያት የዱር እንስሳቱ የውኃ እጥረት እንዳጋጠማቸው አመላክተዋል፡፡

በሀገሬ ቲቪ
2021-12-07