ሀገሬ ቲቪ

‹‹የሚታፈኑ ዜጎች የበዙባት ኢትዮጵያ››

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) እየተበራከተ የመጣው በመንግሥት አካላት የሚደረግ አስገድዶ ዜጎችን መሰወር በአስቸኳይ ይቁም አለ።ዛሬ ከሰዓት ባወጣው መግለጫ ብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞን ፣አቶ ናፖሊዮን ገ/ኢየሱስ ከጋዜጠኞች እና ከማህበረሰብ አንቂዎች ደግሞ አቶ ሰለሞን ሹምዬ፣አቶ ታዲዮስ ታንቱ፣መስከረም አበራ፣ቲና በላይ፣አሸናፊ አካሉ እና ሌሎችም መታሰራቸውን ባሰባሰብኩት መረጃ አረጋግጫለሁ ብሏል።

መብቶችን የአለአግባብ የሚገድብ እና አደጋ ላይ የሚጥል በመሆኑ የፌደራል እና የክልል መንግሥታት በጸጥታ አካላት የለአግባብ የሚታፈኑ ዜጎችን በአስቸኳይ እንዲያስቆሙ ድርጊቱን የፈጸሙት ደግሞ ለህግ እንዲቀርቡ ጠይቋል።በመግለጫው በኦሮሚያ እና በደቡብ ክልል በጸጥታ አካላት የሚደርሱ ጥፋቶችን በዝርዝር በማስቀመጥ መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጠይቋል።በተጨማሪም አላግባብ እስሮች ፣ በኑሮ ውድነት ፣አላስፈላጊ የትራንስፖርት የታሪፍ ጭማሪ እና መሰል ችግሮች ላይ መንግሥት በትኩረት እንዲከታተል እና መፍትሄ እንዲያበጅ አሳስቧል።

በፍሬህይወት ታደሰ
2022-05-23