የአማራ ክልል በተለያዩ ወንጀሎች የተጠረጠሩ 4 ሺሕ 552 ተጠርጣሪዎችን በሕግ ቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ። የክልል የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ ደሳለኝ ጣሰው የክልሉን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል።
በቁጥጥር ስር ከዋሉት ከ40 በላይ የሚሆኑት በፍርድ ቤት ተፈርዶባቸዋል፤ 210 የሚሆኑት ደግሞ በነፍስ ግድያ የተጠረጠሩ መሆናቸው በመግለጫው ተገልጿል። ትክክለኛውን የፋኖ ስም የማይወክሉ፣ በፋኖ ስም ተደራጅተው በሕዝብ ላይ ሕገ ወጥ ድርጊት የሚፈጽሙ ቡድኖችን መንግሥት እንደማይታገስም አስታውቋል።
በመቅደስ እንዳለ
2022-05-23
