ሀገሬ ቲቪ

የደቡብ ኮሪያው ሃዩንዳይ ኢንቨስትመንት

ሀዩንዳይ ሞተር ግሩፕ በአሜሪካ እስከ ፈረንጆቹ 2025 አምስት ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስት አደርጋለሁ አለ። ግሩፑ ከአሜሪካ ኩባንያዎች ጋር በሮቦቲክስ ፣ በበራሪ መኪኖች፣ ያለ ሹፌር ጣልቃገብነት በሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች እና በሰውሰራሽ የማሰብ ችሎታ ላይ ያለውን ትብብር ለማጠናከር አቅዷል።

የደቡብ ኮሪያው ሃዩንዳይ በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የመጀመሪያውን የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ (ኢቪ) እና የባትሪ ማምረቻ ፋብሪካዎችን ለመገንባት እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ ሮይተርስ ጽፏል። በጆርጂያ በወደብ ከተማ ሳቫና አቅራቢያ በ2,923 ሄክታር መሬት ላይ ለመገንባት አስቧል ሲል ፎርብስ ዘግቧል።ፋብሪካው ሙሉ በሙሉ ወደ ስራ ሲገባም ከ 8,000 በላይ ለሚሆኑ ስራተኞች የእንጀራ ገመድ ይሆናል ተብሏል።

በመቅደስ እንዳለ
2022-05-23