የአፍሪካ ልማት ባንክ በአፍሪካ የምግብ ቀውስን ለመከላከል የ1ነጥብ5 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ አፀደቀ። ከ1ነጥብ5 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ውስጥ 11 ሚሊዮን ቶን ስንዴ ፣ 18 ሚሊዮን ቶን በቆሎ፣ 6 ሚሊዮን ቶን ሩዝ እና 2ነጥብ5 ሚሊዮን ቶን አኩሪ አተር ለማምረት ውጥን ተይዟል ።
ድጋፉ 20 ሚሊዮን አነስተኛ ይዞታ ያላቸው አፍሪካውያን አርሶ አደሮች ዘር እንዲያገኙ እና የማዳበሪያ አቅርቦትን በማሳደግ 38 ሚሊዮን ቶን ምግብ በፍጥነት እንዲያመርቱ ያስችላቸዋል ተብሎለታል።ባንኩ ባወጣው መግለጫ በሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት የተነሳ የምግብ አቅርቦት መስተጓጎልን ተከትሎ አፍሪካ በአሁኑ ወቅት ቢያንስ 30 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን የምግብ እጥረት አጋጥሟታል ብሏል ።
በመቅደስ እንዳለ
2022-05-23
