ለስኳር ግዥ ሰባት ድርጅቶች የቴክኒክ እና የፋይናንስ ሰነዳቸውን ቢያስገቡም 2ቱ ተሰርዘዋል ተባለ፡፡
በተከፈተው የ200 ሺሕ ሜትሪክ ቶን ስኳር ግዥ ላይ ሁለቱ ኩባንያውች የተሟላ ሰነድ ባለማቅረባቸው ወዲያው መሰረዛቸው ታውቋል፡፡
የዘርፉ ባለሞያዎች መንግስት ከዚህ በፊት በ600 ሺ ሜትሪክ ቶን የስንዴ ግዢ ላይ ተስተውሎ የነበረ ማጭበርበር ወይም የግዥ መጓተት እንዳይፈጠር ይጠንቀቅ ብለዋል፡፡
ለፋይናንስ ሰነድ መከፈት ካለፉት 4 ኩባንያዎች ሦስቱ ማለትም አግሮኮርፕ፣ ኢዲ ኤንድ ኤፍ ማን እና ሱክደን የተባሉ የሲንጋፖር፣ ብሪታንያ እዲሁም ፈረንሳይ ኩባንያዎች በመሰል የሸቀጥ ጨረታ የሚታወቁ ናቸው፡፡ ሆኖም አዲስ ከተባለው የአሜሪካ ኩባንያ አንጻር ከፍ ያለ ዋጋ ማቅረባቸው ታውቋል፡፡
ሆኖም ምርቱን ከህንድ አልያ ከተባበሩት ኢምሬቶች ወይም ታይላንድ እንጭናለን ያሉ ሲሆን፤ ለወደብ ላይ ፍተሻ 20 ሺሕ ዶላር መድበዋል፡፡
በፍሬህይወት ታደሰ
2022-05-24
