96 ቢሊዮን ብር ካፒታል ላስመዘገቡ ዳያስፖራዎች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ተሰጠ፡፡
በ2014 በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት 96.7 ቢሊዮን ብር ካፒታል ላስመዘገቡ 750 ዳያስፖራዎች የኢንቨስትመንት ፈቃድ መሰጠቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት 750 የዳያስፖራ አባላት በንግድ፣ በኢንቨስትመንት እና በቱሪዝም እንዲሳተፉ የተለያዩ ድጋፎችን ተስጥቷል፡፡
97.6 ቢሊዮን ብር ካፒታል ላስመዘገቡ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ለመሳተፍ ፍላጎት ላላቸው አንድ ሺሕ 489 ዳያስፖራ አባላት የተለያዩ ድጋፎች መደረጉን የሚኒስትሩ መረጃ ያሳያል፡፡
በፍሬህይወት ታደሰ
2022-05-24
