ሀገሬ ቲቪ

የጦጣ ፈንጣጣ ስጋት በኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የጦጣ ፈንጣጣ ስርጭት ስጋት አለን አለ፡፡

ቫይረሱ ከዚህ በፊት ፈንጣጣ መሰሉ በሽታ ተጠቂ የሌለባቸው ሀገራት ሳይቀር እየተስፋፋ መሆኑን የገለጹት በኢንስቲትዩት የቅድመ ማስጠንቀቂያ እና መረጃ ስርዓት አስተዳደር ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ዘውዱ አሰፋ ናቸው፡፡

በኢትዮጵያ የመግቢያ እና መውጫ በሮች ላይ የተለመደው ክትትል እየተደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡ በሀገሪቱ የየብስ እና የአየር ትራንስፖርት መግቢያ እና መውጫ ላይ ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገባ እና ወደ ሌሎች ሀገራት እንዳይሄድ የተላላፊ በሽታዎች ክትትል እየተደረገ መሆኑን ሰምተናል፡፡

የበሽታው ተጠቂ በኢትዮጵያ ቢገኝ ማድረግ ስለሚገባን ስራዎች፣ ለህብረተሰቡ መሰጠት ስለሚገባው የግንዛቤ ፈጠራ መልዕክት እና የህክምና ክትትል ስራዎችን ለመለየት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰራ ነው ተብሏል፡፡

በፍሬህይወት ታደሰ
2022-05-24