የግብጹ ፕሬዚደንት አብዱልፈታህ አልሲሲ በሀገሪቷ የተከሰተው የዋጋ ንረት ተከትሎ ሕዝቡን የዛፍ ቅጠል ብሉ ማለታቸውን ሚድል ኢስት ሞኒተር አስነብቧል፡፡
የግብፅን ሕዝብ ለማረጋጋት ባደረጉት ሙከራ ነብያችን እንዳደረጉት ሁሉ ከዛፍ ላይ ቅጠል ብሉ ሲሉ መክረዋል፡፡
አል-ሲሲ በመቀጠል በአስቸጋሪ ወቅት አማኞች ቅሬታ አላቀረቡም በማለት ግብፃውያን በትዕግስት እንዲጠብቁ እና አፋጣኝ መፍትሄ እንዳይጠይቁ ጠቁመዋል፡፡
በመጋቢት ወር ግብፅ በስድስት ዓመታት ውስጥ ለሦስተኛ ጊዜ ብድር ለማግኘት ወደ አይ.ኤምኤፍፊቷን አዙራለች፡፡
ሀገሪቱ በሙስና ፣በዓለም አቀፉ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እና አሁን በዩክሬንናየሩስያ ጦርነት ስጋት ደቅኖባታ፡፡
በፍሬህይወት ታደሰ
2022-05-24
