የሳይንስ ሊቃውንት በጨረቃ አፈር ውስጥ ተክሎች ለመጀመሪያ ጊዜ ማብቀል ችለናል አሉ፡፡
የአፈር ናሙናዎቹ ወይንም (የአቧራ ናሙናዎቹ) 1969 እስከ 1972 በአፖሎ ተልእኮዎች ወቅት የተሰበሰቡ ናቸው፡፡
የዘሯቸው ዘሮች ከሁለት ቀናት በኋላ የመብቀል አዝማሚያ ማሳየታቸውን በናሳ የገንዘብ ድጋፍ የፍሎሪዳ ዩኒቨርሲቲ ሳይንቲስቶች ገልጸዋል፡፡
ጥናቱ ለረጅም ጊዜ የጠፈር ምርምር እና በምድር ላይ የግብርና ፈጠራ ላይ ከፍተኛ አንድምታ አለው ይላል ናሳ፡፡
የሰው ልጅ በጨረቃ ረዘም ላለ ጊዜ መቆየት የሚያስችል መሆኑን ማሳወቅ የሚያስችል እርምጃም መሆኑ በኮሚዩኒኬሽን ባዮሎጂ ላይ የታተመው የጥናት ውጤት አሳይቷል፡፡
በፍሬህይወት ታደሰ
2022-05-24
