ሀገሬ ቲቪ

ያልተገባ ሀብት ያከማቹት ነጋዴዎች

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሀገራችን በተደራረቡባት ዘርፈ ብዙ ችግሮች : በአቋራጭ ባለፉበት ሀብት መክበር በሚፈልጉ ነጋዴዎች እንዲሁም በሸማቹና በነጋዴው መሀከል ባሉ ደላሎች አማካኝነት ኑሮ ከህብረተሰቡ አቅም በላይ ሆኗል።

የእለት ተዕለት የዋጋ ንረት መጨመር በተቃራኒው የህብረተሰቡ ገቢ ባለበት መቆም የሀገሬን ህዝብ አልቻልኩም ከአቅሜ በላይ ሆኗል እንዲል አስገድዶታል።

ከሀገራችን ችግር አልፎም አለም እያስተናገደችው ያለው የፀጥታ ችግር ሀገራችን ኢትዮጵያን ልትቋቋመው ያለቻለችው የኑሮ ውድነት ውስጥ ከቷታል። ለአብነትም ከተጀመረ ወራቶችን ያስቆጠረውን የሩሲያና የዩክሬንን ቀውስ ማንሳት ይቻላል።

በዚህ ጉዳይ ላይ የካ ክፍለ ከተማ ኮሚዩኒኬሽን ፅህፈት ቤት በኑሮ ውድነትና መፍትሔው ዙሪያ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር የፖናል ውይይት መድረክ ያዘጋጀ ሲሆን በመድረኩም ለሀገሪቱ የኑሮ አለመረጋጋት መከሰት በርካታ ምክያቶች ቢነሱም ከአቅም በላይ ትርፍ ለማግኘት የሚሹ አንዳድ ነጋዴዎች ዋነኛ ምክንያት ሆነዋል ተብሏል።

እንደ የካ ክፍለከተማ ያልተገባ የዋጋ ጭማሬ ያደረጉ 77 ሱቆች ታሽገዋል። ነገር ግን ከንዳንድ ስግብግብ ነጋዴዎችም ባለፈ ለዚህ ጉዳይ ገበሬው ጋር ሔደው በመደራደር ከአምራች ወደ ሸማች እናደርሳለን በሚል በከተማችን ያለፍቃድ የተሰማሩ ህገወጥ ደላላዎች ሌላኛው ለሀገሪቷ ራስ ምታት ሲሆኑ እርምጃ እየተወሰደባቸው መሆኑ ተጠቁሟል።

በ አገር አቀፍ ደረጃ አሳሳቢ የሆነውን የኑሮ ውድነት በቋሚነት ለመቅረፍ ያልትገባ ሀብት ለማከበት በሚሹ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ በመውሰድ : ነጋዴው ለገበያ ያወጣውን እቃ ከየት ምንጩን በማጣራት ላይ በስፋት እየተሰራ ነው ተብሏል ።

ሸማቹ የእሁድ ገበያዎችን እንዲጠቀም በማሳወቅ እንዲሁም በየቤቱ የተከማቹ የመገልገያ እቃዎች ላይ ፍተሻ በማድረግ ከመንግስት የሚቀርቡ ድጎማዎችን በመጨመር በክፍለከተማው ኑሮን ለማሻሻል ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ መሆኑ በውይይቱ ተገልጿል።

በዮሴፍ ከበደ
2022-05-24