ታይም መጽሔት የ 2022 መቶ ተጽዕኖ ፈጣሪዎችን ከቀናት በፊት ይፋ ባደረገበት ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድን አካትቶ ነበር።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከኤርትራ ጋር የሰላም ስምምነት በማድረግ የኖቤል ሽልማት መቀበላቸውን መጽሔቱ አስታውሷል።
ስምምነቱ ታዲያ ለኢትዮጵያ የእርስ በእርስ ጦርነት ዘር የተከለበት ነዉ'' ሲል ገልጾታል።
መጽሔቱ እንደገለጸው ከሆነ 19ኛው ወሩን ባስቆጠረው የእርስ በርስ ጦርነት የመንግሥት ኃይሎች በጅምላ ግድያ፣ ጾታዊ ጥቃት እና የዘር ማጽዳት ክስ ቀርቦባቸዋል።
ይህን የታይም መጽሄት ገለጻ ኢትዮጵያ እንደማትቀበለው ማስታወቋን ዘስታር የተሰኘው የዜና ምንጭ ጽፏል።
ለመጽሄቱ በተላከው ደብዳቤ የህወሓትን ትርክት ያስተጋባ እና ታስቦበት የጠቅላይ ሚንስትሩን ስም ለማጥፋት የተደረገ ነው መባሉን የዜና ምንጩ ዘግቧል።
በሙሉጌታ በላይ
2022-05-25
