የፊዚክስ ሊቃውንቶች ልዩ የሆነ ተሻጋሪ የድምፅ ሞገድ ማግኘታቸውን አስታወቁ፡፡ የሆንግ ኮንግ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች ናቸው አዲስ ዓይነት የድምፅ ሞገድ ያገኙት ፡፡ አዲስ ተገኘ የተባለው የአየር ወለድ የድምፅ ሞገድ በተቃራኒ አቅጣጫ ከሌሎች ሞገዶች በተለየ ይንቀጠቀጣል፡፡ ሞገዱ ሁለቱንም የአከርካሪ እና የምህዋር ማዕዘን ፍጥነት እንደ ብርሃን እንደሚሸከም ተነግሯል። ግኝቱ ተመራማሪዎች ስለ ድምፅ ሞገድ የነበራቸው እምነት መቀየሩም ተገልጿል፡፡ ይህም መተግበሪያዎች በውኃ ውስጥ መልእክት መላክ እና መቀበል እንዲችሉ እንዲሁም ምስሎችን መጠቀም ለማስቻል ይረዳሉ ተብሏል ፡፡ የሞገዱ መገኘት አዳዲስ መተግበሪያዎች ለመፍጠር በር ይከፍታልም ተብሎ ይጠበቃል።
በሀገሬ ቴቪ
2021-12-09
