ዓለምአቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተማጓች (ሲፒጄ )የኢትዮጵያ መንግሥት ያለአግባብ የታሰሩ ጋዜጠኞችን ይፍታ አለ።
በኢትዮጵያ በቅርቡ የታሰሩት 11 ጋዜጠኞችና እና የሚዲያ ሰራተኞች በአስቸኳይ እንዲለቀቁ ጠይቋል።
ኮሚቴው መንግሥት፤ ባለስልጣናት በሚዲያ ባለሙያዎች ላይ የሚያደርጉትን ማስፈራራት ያስቁም ሲልም ጠይቋል።
ሲፒጄ የአማራ ክልል መንግሥት እያካሄደ ባለው “የህግ ማስከበር ዘመቻ” ከግንቦት 11 ጀምሮ በአማራ ክልል እና በአዲስ አበባ 11 ጋዜጠኞች እና የሚዲያ ባለሙያዎች መያዛቸውን ባውጣው ሪፖርት ገልጿል።
በክልሉ በህገወጥ እንቅስቃሴ ተጠርጥረው 4 ሺሕ500 ሰዎች መያዛቸውንም ጨምሮ ጠቅሷል።
በፍሬህይወት ታደሰ
2022-05-25
