ኬኒያ የኢትዮጵያ ከአሜሪካው ቀረጥ ነፃ የገበያ ዕድል አጎዋ መታገድ 10 ቢሊዮን የኬኒያ ሽልንግ አስገኝቶልኛል አለች።
ኬንያ በፈረንጆቹ 2022 ከአጎዋ ኢትዮጵያ በመሰረዟ በመጀመሪያዎቹ ሶስት ወራት ወደ አሜሪካ የላከችው ምርት ከ1.4 ቢሊዮን ሽልንግ ወደ 14.8 ቢሊዮን ሽልንግ ከፍ ብሏል።
ከኢትዮጵያ ወደ አሜሪካ ይላኩ የነበሩ በርካታ ምርቶች አሁን አይላኩም እኛም ይህንን እድል ተጠቅመን ወደ ገበያው የምናስገባቸውን ምርቶች በ25 በመቶ ከፍ አድርገን እየላክን ነው ሲሉ የሀገሪቱ የኢንዱስትሪ፣ ንግድና ኢንተርፕራይዝ ልማት ካቢኔ ፀሐፊ ቤቲ ማና ተደምጠዋል። ዘገባው የዘ-ኢንሳይደር ነው።
በሳምሶን ገድሉ
2022-05-25
