ሀገሬ ቲቪ

‹‹አይጥ በበላ ዳዋ ተመታ››

የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ በሩሲያ ላይ በተጣለ ማዕቀብ ምክንያት በዳርቻው ላይ ያሉ ሀገራት እየተሰቃዩ ነው አሉ። በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ያልተቋረጠ የኢኮኖሚ ችግር እየተጋፈጠች ያለችው አፍሪካ ከሩሲያ የዩክሬን ወረራ ጋር በተገናኘ የምግብ ዋጋ መጨመር ክፉኛ ተመታለች።

የአፍሪካ ህብረት በሞስኮ እና በኪዬቭ መካከል ውይይት እንዲፈጠር ተልዕኮ ሲያዘጋጅ ውይይት እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል። ራማፎሳ የተናገሩት የጀርመኑ መራሂተ መንግሥት ኦላፍ ሾልስ ደቡብ አፍሪካን በጎበኙበት ወቅት ነው። ወደ አህጉሪቱ ባደረጉት የመጨረሻ ጉዞ ለዩክሬን ዲፕሎማሲያዊ ድጋፍን ማሰባሰብን ዓላማው አድርጓል።

በፍሬህይወት ታደሰ
2022-05-25