ሀገሬ ቲቪ

እለቱን ከታሪክ-የአፍሪካ ቀን

የዛሬዋ እለት የአፍሪካ ቀን ተብላ ትጠራለች፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ከ69 አመታት በፊት የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የተመሰረተው በዛሬዋ እለት ነውና፡፡ በኛዋ መዲና አዲስ አበባ ቀዳማዊ ሃይለ ስላሴ ከሰላሳ ሃገራት የመጡ የአፍሪካ መሪዎች በተገኙበት የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ተመሰረተ፡፡

ቀደም ብላ የአፍሪካ የነጻነት ቀን ተብላ ትጠራ የነበረችው የዛሬዋ እለት የአፍሪካ ቀን ተብላ ተሰይማለች። በዚህች እለት በ1955 የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ከመመስረቱ አስቀድሞ በጋና ዋና ከተማ በጋናው ጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር ክዋሜ ንኩርማህ ጋባዥነት ነጻ የአፍሪካ ሃገራት ተሰባስበው መነጋገር ቻሉ።

በዚሁ የሃገራቱ ስብሰባ የአፍሪካ ሃገራት ነጻ መውጣት አለባቸው የሚለው ሃሳብ በሰፊው ተንጸባርቋል። ከአምስት አመታት በኋላ ሁለት ሶስተኛው የአፍሪካ ሃገራት ነጻ በወጡበት የአፍሪካ ሃገራት መሪዎች በአዲስ አበባ ተሰባሰቡ። ነጻ ከወጡት 32 ሃገራት 30ው በተገኙበት የአፍሪካ አንድነት ድርጂትን ቻርተር ተፈራረሙ፡፡

የአፍሪካ አንድነት ድርጅት በምስረታው የአፍሪካ የነጻነት ተዋጊዎችን ለማገዝ እና የሃገራቱን የነጻነት ሂደት ለማፋጠን ሃገራቱ ተስማምተውበታል። ከዚህ በተጨማሪም የአፍሪካውያንን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል ቃል የገቡበትም ነበር። በጊዜው ንግግር ያደረጉት ቀዳማዊ ሃይለ ስላሴም ስምምነቱ ለሺህ አመታት ሊቆይ ይችላል ሲሉ ተደምጠዋል።

ድርጂቱ መጀመሪያ ላይ የአንጎላ፥ ሞዛምቢክ፥ ደቡብ አፍሪካ እና ደቡብ ርሆዴሽያን ነጻነት ለማፋጠን ግቡ አድርጓል። በ1994 በደቡብ አፍሪካ ደርባን የአፍሪካ አንድነት ድርጂት ስሙን ወደ አፍሪካ ህብረት ቀይሯል።

ታዲያ ከዛን ጊዜ ጀምሮ የተለያዩ መሪ ቃሎችን በመጠቀም በየአመቱ ሚይ 25 የሚከበረው የ አህጉራችን አፍሪቃ ቀን ዛሬ ላይ ደርስዋል።

በአብርሃም በለጠ
2022-05-25