‹‹ቀን ይጥላል ቀን ያነሳል›› ይላል የሀገር ሰው ከዕለታት በአንዱ ቀን ቀን የጣለው አብዮት ከአባቱ ጋር ኑሮን ለማሸነፍ ከጎንደር ወደ አዲስ አበባ ይመጣሉ፡፡ አዲስ አበባ ለአንዱ የተመቸች ለአንዱ የከፋች ትሆንና የእለት ጉርሱን የሚያደርሱት አባት ፍሰሃ ከልጃቸው ሞት ይለያቸዋል፡፡ ህጻኑ አሳዳጊ በማጣት ጎዳና ላይ ይወጣል፡፡ ጎዳና ላይ ያዩት በማዘን ማሳደጊያ ያስገቡታል በወቅቱ የተስፋ ለህጻናት ድርጅት መስራች ወይዘሮ የወይንእሸት ማስረሻ ልጁን ተቀብለው ከሌሎች ልጆች ጋር ቀላቅለውታል፡፡
የዛኔው ልጅ የአሁኑ ወጣት በህይወት ቆይቶ ይህን ለመመስከር በቅቷል፡፡
“ተስፋ ለህጻናት በኔ ህይወት ላይ ትልቅ ቦታ አለው፡፡እኔ የተሰራሁት በዚህ ድርጅት ነው፡፡ ሰው ስትሆኚ ሰው ይርብሻል ያንን ያስታገስኩበት ድርጅት ነው፡፡”
ተስፋ ለህጻናት ወይዘሮ የወይንእሸት ማስረሻ በተባሉ በአንዲት በጎ አሳቢ በፈረንጆቹ በ2001 ከዛሬ 22 ዓመታት በፊት በኤች አይቪ ወላጆቻቸውን ያጡ እና ለአደጋ የተጋለጡ ህጻናትን ለመንከባከብ ዓለማው አድርጎ ተቋቋመ፡፡
ድርጅቱ ከ1 ሺሕ በላይ ህጻናትን እና እናቶችን በመርዳት በማስተማር ዛሬ ላይ ለፍሬ መብቃታቸውን ያደጉበትን ቤት የሚያገለግሉም እንዳሉ ተመልክተናል፡፡
በተስፋ ለህጻናት ድርጅት የስፖንሰርሺፕ ፕሮግራም አስተባባሪ ወ/ሮጸዳል እንድሪያስእንዳሉት ከሆነ “ትምህርት ቤት መሄድ የማይችለው ትምህርት ቤት ሆደ የተመረቁ ለፍሬ የበቁትን ስናይ ደስ ይለናል፡፡ለዚህም ምስክር የሚሆነው እዛው ያደጉ ልጆች መልሰው በድርጅቱ ውስጥ ተቀጥረው እያገለገሉ ነው፡፡›”
ድርጅቱ እኔን እና መሰል ችግር የገጠማቸውን ከውድቀት አንስቶ ወደ መልካምነት ቀይሮናል በጎዳና ከመኖር ታድጎ ለፍሬ አብቅቶ ዛሬ የድርጅቱ ሰራተኞች ለመሆን በቅተናል ይላል አብዮትፍሰሃ ፡፡
አሁን ላይ ከ120 በላይ ልጆች እስኪመረቁና እራሳቸውን እሲኪችሉ ድረስ የትምህርት፣የአልባሳት፣የጤና፣የንጽህና መጠበቂያ በስፖንሰር በኩል ድጋፍ ይደረግላቸዋል፡፡ የኑሮ ውድነት የፈተነው ድርጅቱ እንደቀድሞ በርካታ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ውስጥ ልጆችን ማስጠለል ባልችልም 1 ቤት እና 10 ልጆችን እየደገፍኩ ነው ብሏል፡፡ መንግሥት ይመልከተን ሲል ጥሪ አቅርቧል፡፡
በቋሚነት ከሚሰራው በተጨማሪ ተስፋ ለህጻናት ሰብአዊ አገልግሎት ውሎና አዳራቸውን ጎዳና ላይ ያደረጉ ወጣቶችና ልጅ ያቀፉ ህጻናትን የመደገፍ እና በዘላቂነት የማቋቋም ፕሮግራም በመጀመር በ2 ዙር አሰልጥኖ በማስመረቅ ወደ ስራ ማሰማራቱን ሰምተናል፡፡
በፍሬህይወት ታደሰ
2022-05-25
